አንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሚቀጥሉት ሳምንታት 41 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊደርስ የሚችል የሙቀት መጠን እንደሚያስተናግዱ ተነገረ
18:22 14.03.2026 (የተሻሻለ: 18:24 14.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሚቀጥሉት ሳምንታት 41 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊደርስ የሚችል የሙቀት መጠን እንደሚያስተናግዱ ተነገረ
በሚቀጥሉት ሳምንታት የጋምቤላ፣ የአፋር፣ የሶማሌ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እንዲሁም የአማራ ክልል ምዕራባዊ ዞኖች ዕለታዊ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ33 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊደርስ እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
በወሩ ውስጥ የሚታየው ጠንካራ የቀን ፀሐይ ሃሩር ሞቃታማ ሌሊት እንደሚያስከትል ተጠቁሟል።
ይህ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በሰውና በእንስሳት ጤና እንዲሁም በውሃ ሀብት ላይ ጫና ሊፈጥር ስለሚችል ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።
በሌላ በኩል የግብርና አካባቢዎች በጠንካራ የደመና ስብስቦች ምክንያት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጿል።
ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍሎች ከሚጠበቀው ዝናብ 30 በመቶ ያህሉን፣ መካከለኛውና ምስራቃዊው ክፍል ደግሞ ከ20 እስከ 40 በመቶ የሚሆነውን ዝናብ እንደሚያገኙ ተተንብይዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X