ኢትዮጵያ በቁልፍ ማዕድናት ልማት ዙሪያ የ2 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ፈቃድ ሰጠች
14:36 14.03.2026 (የተሻሻለ: 14:44 14.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በቁልፍ ማዕድናት ልማት ዙሪያ የ2 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ፈቃድ ሰጠች
የማዕድን ሚኒስቴር ለወርቅ፣ ብረት እና ፖታሽ አምራች ኩባንያዎች የምርት ፈቃዱን ሰጥቷል።
ፈቃድ የተሰጣቸው አካላት፦
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ፦ በአፋር ክልል የፖታሽ ማምረቻ ፈቃድ የተሰጠው ሲሆን በሁለት ዓመት ዉስጥ የፋብሪካ ግንባታውን ጨርሶ ወደ ምርት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
ዜድዋይቲ ቢዲአይኤም (ZYT BDIM)፦ በተመሳሳይ የተሰጠው የሁለት ዓመት ፋብሪካ የመገንቢያ ግዜ በመጠቀም የብረት ማዕድን እንዲያመርት ፈቃድ ተሰጥቶታል።
ቤሮ ማይኒንግ፦ ለወርቅ ማምረቻ ፈቃድ ተሰጥቶታል። ኩባንያው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የፋብሪካ ግንባታውን ጨርሶ ወደ ምርት ሥራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ፤ “ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቶቿን በማልማት ለሀገር ዕድገት ማዋል የሚያስችል ትልቅ እርምጃ እየወሰደች ነው ሲሉ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ተናግረዋል።
ፈቃድ የተሰጣቸው ሦስቱ አልሚዎች 4.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስትመንት እንዳስመዘገቡ ከማዕድን ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia