በጋሞ ዞን የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ የሦስት ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ
12:37 14.03.2026 (የተሻሻለ: 12:44 14.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በጋሞ ዞን የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ የሦስት ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ
ብሔራዊ የሐዘን ቀኑ ከመጋቢት 05 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።
በእነዚህ ቀናት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች፣ በኤምባሲዎች እና በቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ዝቅ ብሎ ይውለበለባል።
መጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ እስካሁን የ80 ወገኖች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል። የቀሪዎቹን ለማግኘት ፍለጋው መቀጠሉም ተጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X