የደቡብ ሱዳን ጦር በጆንግሌ ግዛት የምትገኝ ወሳኝ ምስራቃዊ ከተማን በቁጥጥር ስር አዋለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየደቡብ ሱዳን ጦር በጆንግሌ ግዛት የምትገኝ ወሳኝ ምስራቃዊ ከተማን በቁጥጥር ስር አዋለ
የደቡብ ሱዳን ጦር በጆንግሌ ግዛት የምትገኝ ወሳኝ ምስራቃዊ ከተማን በቁጥጥር ስር አዋለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.03.2026
ሰብስክራይብ

የደቡብ ሱዳን ጦር በጆንግሌ ግዛት የምትገኝ ወሳኝ ምስራቃዊ ከተማን በቁጥጥር ስር አዋለ

የመንግሥት ኃይሎች ስትራቴጂያዊ የሆነችውን የአኮቦ የድንበር ከተማ ነፃ ማውጣታቸውን፣ ከ50 በላይ አማፂያንን መግደላቸውን እንዲሁም በርካታ ተሽከርካሪዎችንና ከባድ የጦር መሣሪያዎችን መማረካቸውን የጦር ሠራዊቱ ቃል አቀባይ ጄኔራል ሉል ሩአይ ኮአንግ አስታውቀዋል።

ባለሥልጣናቱ ጥቃቱን ከመሰንዘራቸው በፊት ሲቪሎችና የረድኤት ሠራተኞች እንዲወጡ በማድረጋቸው ምክንያት 200 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከተማዋን ሸሽተዋል። ጄኔራል ሉል ሩአይ ኮአንግ፤ ከተማዋ ዳግም በቁጥጥር ስር መዋሏን ተከትሎ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎችና የሰብዓዊ ረድኤት ድርጅቶችም በአካባቢው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

ግጭቱ ዳግም ያገረሸው እ.ኤ.አ በ2025 የጸደይ ወቅት የተቃዋሚ መሪው ሪየክ ማቻር በሀገር ክህደት ወንጀል መታሰራቸውን ተከትሎ ሚሊሻዎች በርካታ የሰሜን ምስራቅ ከተሞችን በቁጥጥር ስር በማዋላቸው ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የጆንግሌ ግዛት የፋይናንስ ሚኒስትር ዶንጌ ጋይ ዶንጌ በቅርቡ ለስፑትኒክ በሰጡት አስተያየት፤ የስምንት ዓመቱ የሰላም ስምምነት አሁንም በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝና የማይቀለበስ መሆኑን እንዲሁም ምንም እንኳን ግጭቶች ቢኖሩም የመንግሥት ተቋማት መረጋጋት እየታየባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የደቡብ ሱዳን ጦር በጆንግሌ ግዛት የምትገኝ ወሳኝ ምስራቃዊ ከተማን በቁጥጥር ስር አዋለ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የደቡብ ሱዳን ጦር በጆንግሌ ግዛት የምትገኝ ወሳኝ ምስራቃዊ ከተማን በቁጥጥር ስር አዋለ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0