ኬንያ ጉንዳኖችን በድብቅ ለማውጣት የሞከረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዋለች
16:51 13.03.2026 (የተሻሻለ: 16:54 13.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኬንያ ጉንዳኖችን በድብቅ ለማውጣት የሞከረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዋለች
ዣንግ ኬኩን የተባለ ቻይናዊ ማክሰኞ ዕለት በናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኢሚግሬሽን እና በዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣናት በቁጥጥር ስር መዋሉን አንድ የእንግሊዝ የዜና ወኪል ዘግቧል። ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው በፍተሻ ወቅት በህይወት ያሉ ከ2 ሺህ በላይ "ንግስት የጓሮ ጉንዳኖች" በሻንጣው ደብቆ በመገኘቱ ነው።
የእነዚህን ብርቅዬ ንግስት ጉንዳኖች ውስብስብ የአኗኗር ዘይቤ በቅርበት መመርመር በሚሹ የትርፍ ግዜ አሳላፊዎች ምክንያት ነፍሳቶቹ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል፡፡
የኬንያ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ እ.ኤ.አ በ2025 በሺዎች የሚቆጠሩ ጥበቃ የሚደረላቸውን ንግስት ጉንዳኖች ያለፈቃድ በመያዝ፤ ወደ ውጭ ለመላክ በሞከሩ አራት ግለሰቦች ላይ የ7,700 ዶላር ገደማ የገንዘብ ቅጣት አስተላልፏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X