የፌዴራል ፖሊስ የጣት አሻራ አሰጣጥን ወደ ዲጂታል ሊቀይር ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየፌዴራል ፖሊስ የጣት አሻራ አሰጣጥን ወደ ዲጂታል ሊቀይር ነው
የፌዴራል ፖሊስ የጣት አሻራ አሰጣጥን ወደ ዲጂታል ሊቀይር ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.03.2026
ሰብስክራይብ

የፌዴራል ፖሊስ የጣት አሻራ አሰጣጥን ወደ ዲጂታል ሊቀይር ነው

🫆 የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራና መከላከል ሥራውን ይበልጥ ለማዘመን ከብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የተሳሰረ የዲጂታል የጣት አሻራ አሰጣጥ ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል።

ይህ አዲስ አሠራር ወንጀለኞችን በቀላሉ ለመለየት፣ የትራፊክ ቁጥጥርን ለማቀላጠፍና የማንነት ማጭበርበርን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፤ “የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ህብረተሰቡ ለሥራ ቅጥር፣ ለፓስፖርትና ለልዩ ልዩ ሰነዶች የሚያወጣውን የአሻራ አገልግሎት ከብሔራዊ ፋይዳ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር በማኑዋል ይሠራ የነበረው የአሻራ አሰጣጥ ሥርዓት በቅርቡ ወደ ዲጂታል ይቀየራል” ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0