በኢትዮጵያ ከእንሰት ቃጫ የተሠራ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ለገበያ ቀረበ
15:29 13.03.2026 (የተሻሻለ: 15:34 13.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ ከእንሰት ቃጫ የተሠራ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ለገበያ ቀረበ
የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ግብዓት (ከእንሰት ቃጫ እና ከጥጥ ጨርቅ) የተዘጋጀ አዲስ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ምርት ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል።
🩹 ምርቱ ከኬሚካል ንክኪ የፀዳ፣ ታጥቦ ድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውልና አካባቢን የማይበክል በመሆኑ በተለይ አቅም ለሌላቸው ወገኖች ትልቅ እፎይታ እንደሚሆን መገለፁን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘገባ አመላክቷል።
ይህ አዲስ የፈጠራ ውጤት ችግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት ቢሆንም፤ ምርቱን በስፋት ለማሰራጨት የማምረቻ መሳሪያዎች እጥረት ስላለበት የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ተመራማሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X