ሄዝቦላህ አጸፋዊ እርምጃ ወሰደ - የእስራኤል "አይረን ዶም" ተጨናነቀ

ሰብስክራይብ

ሄዝቦላህ አጸፋዊ እርምጃ ወሰደ - የእስራኤል "አይረን ዶም" ተጨናነቀ

​ሄዝቦላህ የእስራኤልን ዝነኛ የአየር መከላከያ ስርዓት "አይረን ዶም" የሰበሩ መጠነ ሰፊ የሮኬት ጥቃቶችን በመሰንዘር ጠንካራ መልዕክት አስተላልፏል። እንደ ኒውዮርክ ፖስት ዘገባ (የእስራኤል መከላከያ ሰራዊትን ጠቅሶ)፣ በአንድ ቀን ውስጥ ከተተኮሱ 100 ገደማ ሚሳኤሎች መካከል ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው መክሸፍ የቻሉት።

​ይህ የሆነው በአንድ አጋጣሚ በተፈጠረ ክፍተት ነው ወይስ አዲስ የሄዝቦላህ ስልት መጀመሪያ?

  አይረን ዶም ለምን ከሸፈ?

​"እ.ኤ.አ. በ2024 እስራኤል ለሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢዎች እጅግ የተጠጋጉ  የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ሽፋን አስቀምጣ ከነበረበት ሁኔታ በተለየ፣ አሁን ላይ ግን ከኢራን የሚሰነዘሩ የድሮን ጥቃቶችን እና መሰል ስጋቶችን ለመከላከል ሲባል ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአየር መከላከያ ስርዓቷን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አሰራጭታለች። በዚህም ምክንያት በሰሜን በኩል ያለው የመከላከያ ጥንካሬ በአጠቃላይ ደክሟል" ሲሉ ሩሲያዊው ወታደራዊ ታዛቢ ዩሪ ሊያሚን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

​አክለውም፣ የእስራኤል አየር ኃይል አብዛኛው ክፍል በኢራን ግንባር ላይ በተሰማሩ ዘመቻዎች መጠመዱ፣ ለሊባኖስ ግንባር የሚሆን አነስተኛ ሃብት ብቻ እንዲኖር አድርጎታል ብለዋል።

  የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በጀት አሁን ያለውን ጦርነት መሸከም ይችላል?

​የታሚር የሚሳኤሎች መቃወሚያን በተመለከተ፣ እነዚህ ሚሳኤሎች የሚመረቱት በእስራኤሉ ራፋኤል እና በአሜሪካው አርቲኤክስ ኮርፖሬሽን ትብብር ሲሆን፣ አብዛኛው የማምረት ሂደት ደግሞ በአሜሪካ ውስጥ የሚከናወን መሆኑን ሊያሚን ያብራራሉ።

​"ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ ዓመት መገባደጃ ላይ የታሚር የሚሳኤሎች መቃወሚያን ለማምረት አርካንሳስ ውስጥ አዲስ ፋብሪካ የተከፈተ ሲሆን፣ ምርቱም በአብዛኛው በአሜሪካ ወታደራዊ እርዳታ የሚደገፍ ነው።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0