በጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት ናዳ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ70 ተሻገረ
18:53 12.03.2026 (የተሻሻለ: 18:54 12.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት ናዳ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ70 ተሻገረ
በዞኑ አራት ወረዳዎች ከባድ ዝናብን ተከትሎ ያጋጠመው አደጋ እስካሁን የታወቁ ጉዳቶች፦
190 ቤቶችን ወድመዋል፡፡
3,480 በላይ የቤተሰብ አባላት ያሏቸው 575 አባወራዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።
በአርባ ምንጭ ከተማ የኩልፎ ወንዝ ሞልቶ አቅጣጫውን በመሳቱ፣ 31 በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ማኅበራት፣ 2 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች እና 1 ግብረ ሰናይ ድርጅት አውድሟል፡፡
የክልሉ መንግሥት በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም የክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይለማሪያም ተስፋዬ ገልፀዋል። አክለውም ለጋሾች እና ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣይ 10 ቀናት ዝናቡ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሜቲዎሮሎጂ ትንበያ ያረጋገጠ ሲሆን፣ በአደጋ ስጋት አከባቢዎች ላይ የሚገኙ ዜጎች አከባቢውን እንዲለቁ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ቢሮው ጨምሮ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X