የኢትዮጵያ ግዙፉ ሚሊኒየም አዳራሽ እየፈረሰ ነው፡- ለአዲስ አበባ አዲስ መልክ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ግዙፉ ሚሊኒየም አዳራሽ እየፈረሰ ነው፡- ለአዲስ አበባ አዲስ መልክ

ላለፉት 18 ዓመታት የኢትዮጵያ የታላላቅ ኩነቶችን ሲያስተናግድ የቆየው ሚሊኒየም አዳራሽ ለታላቅ የልማት ፕሮጀክት ታጭቶ ሊሞሸር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማስፋፊያ ሥራውን በይፋ ጀምሯል።

ኢትዮጵያ በ2027 ለምታስተናግደው 32ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) ዝግጅት ቁልፍ አካል በመሆን በቦታው ላይ "ሞክሲ ባይ ማሪዮት" (Moxy by Marriott) የተሰኘ ዘመናዊ ሆቴል ይገነባበታል።

የመልሶ ግንባታው የአዳራሹን የማስተናገድ አቅም ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ማሳደግን ጨምሮ በርካታ ማሻሻያዎችን ይዟል (ቪዲዮውን ይመልከቱ)፡፡

ታላቁን የኢትዮጵያ ሚሊኒየም በዓል፣ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች፣ ሕዝባዊና ብብሔራዊ በዓላት፣ ሃይማኖታዊ መርሃ ግብሮች፣ የሙዚቃ ድግሶች፣ የንግድ ዐውደ-ርዕዮችን ጨምሮ በርካታ ሁነቶችን ለሁለት አሥርት ዓመታት ያስተናገደው አዳራሹ ከበርካቶች የትዝታ ማኅደር አይጠፋም፡፡

የስፑትኒክ ቤተሰቦች የሚሊኒየም አዳራሽ ትዝታዎን ይንገሩን፤ በነባሩ ቁመናው የሚናፍቁት ከሆነም ሐሳብዎን ያጋሩን

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0