በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚፈጠር መስተጓጎል በመላው አፍሪካ ላይ ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊፈጥር ይችላል - የማኅበረ-ኢኮኖሚ ተመራማሪ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚፈጠር መስተጓጎል በመላው አፍሪካ ላይ ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊፈጥር ይችላል - የማኅበረ-ኢኮኖሚ ተመራማሪ
በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚፈጠር መስተጓጎል በመላው አፍሪካ ላይ ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊፈጥር ይችላል - የማኅበረ-ኢኮኖሚ ተመራማሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.03.2026
ሰብስክራይብ

በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚፈጠር መስተጓጎል በመላው አፍሪካ ላይ ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊፈጥር ይችላል - የማኅበረ-ኢኮኖሚ ተመራማሪ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲው የማኅበረ-ኢኮኖሚ ተመራማሪ መሐመድ ኢብራሂም እንደገለጹት፣ አፍሪካ ከውጭ በሚገባ ነዳጅ እና በዓለም አቀፍ የባሕር ትራንስፖርት መስመሮች ላይ ያላት ጥገኝነት በመካከለኛው ምስራቅ ለሚከሰት አለመረጋጋት ተጋላጭ ያደርጋታል።

ተማራማሪው፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና በውጭ ምንዛሬ እጥረት ተፅእኖ ምክንያት በፍጥነት ይናወጣል ሲሉ የችግሩን ስፋት ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይት አስረድተዋል።

" ይህ ተጋላጭነት አፍሪካ የሀገር ውስጥ የነዳጅ ማጣሪያ አቅሟን በማስፋት የኃይል ዋስትናዋን ማጠናከር እንዳለባት ያመላክታል።" ብለዋል፡፡

መሐመድ አክለውም፣ አኅጉሪቱ የሚያጋጥማትን የኢኮኖሚ መዋዠቅ ለመቋቋም የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና በመጠቀም ጥሬ ዕቃን ብቻ ወደ ውጭ የመላክና የተጣራ የነዳጅ ምርትን ውድ በሆነ ዋጋ የመግዛት ልምዷን መቀየር እንዳለባት ይሞግታሉ።

"የክልላዊ የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማትን እና አኅጉር አቋራጭ የኤሌክትሪክ ትስስርን በማጋራት ቀጣናዊ የኃይል ትብብርን ማጠናከር ... እሴት የሚጨምሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ኢንዱስትሪና አምራች ዘርፍን ማበረታታት ያስፈልጋል" ሲሉ ሃሳባቸውን ደምድመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0