ኢራን የበላይነትን አትፈልግም - የምትሻው ከጎረቤቶቿ ጋር አንድነት እና የጋራ ግንኙነቶች ብቻ ነው - የበላይ መሪው ሞጅታባ ካሜኒ
16:56 12.03.2026 (የተሻሻለ: 17:04 12.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢራን የበላይነትን አትፈልግም - የምትሻው ከጎረቤቶቿ ጋር አንድነት እና የጋራ ግንኙነቶች ብቻ ነው - የበላይ መሪው ሞጅታባ ካሜኒ
“ከጎረቤቶቻችን ጋር ባለን ወዳጅነት እናምናለን፤ ጥቃቶችን የምንፈጽመው በአሜሪካ ወታደራዊ ካምፖች ላይ ብቻ ነው። ይህም የግድ የምንቀጥልበት ጉዳይ ነው” ሲሉ ሞጅታባ ካሜኒ እንደ አዲስ የበላይ መሪ (ራህባር) ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግር ገልጸዋል።
በመሪው የተሰጡ ተጨማሪ መግለጫዎች፦
ኢራን ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር በተደረገው ግጭት ሕይወታቸውን ላጡ ሰማዕታት ተገቢውን የበቀል እርምጃ ትወስዳለች።
የሆርሙዝ ወሽመጥ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ውስጥ እንደ ስልታዊ ቁጥጥር (መደራደሪያ) ሆኖ እንዲያገለግል፣ በኢራን ቁጥጥር ስር መቆየት አለበት።
ቴህራን በቀጣናው የሚገኙ ሀገራት በአካባቢያቸው ያሉ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን በአስቸኳይ እንዲዘጉ ጥሪ ታቀርባለች።
ኢራን ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት መሪዎች ጋር ገንቢ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ትጠብቃለች።
በግጭቱ ወቅት ለደረሱ ጉዳቶች ቴህራን ተገቢው ቁሳዊ የካሳ ክፍያ እንዲፈጸምላት ትጠይቃለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X