በደቡብ ሩሲያ የሚገኘው የሩስካያ የጋዝ መጭመቂያ ጣቢያ በዩክሬን ኃይሎች ጥቃት እንደተሰነዘረበት የጋዝፕሮም ኢነርጂ ኮርፖሬሽን ገለጸ

ሰብስክራይብ

በደቡብ ሩሲያ የሚገኘው የሩስካያ የጋዝ መጭመቂያ ጣቢያ በዩክሬን ኃይሎች ጥቃት እንደተሰነዘረበት የጋዝፕሮም ኢነርጂ ኮርፖሬሽን ገለጸ

​ኩባንያው ስለ ሌሎች ጥቃቶችም የሚከተለውን ብሏል፡-

​ከአንድ ቀን በፊት በቤሬጎቫያ እና ካዛቺያ የጋዝ መጭመቂያ ጣቢያዎች ላይ ጥቃቶች ተመዝግበዋል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከየካቲት 17 ጀምሮ በደቡብ ሩሲያ በሚገኙ የጋዝፕሮም ተቋማት ላይ 12 ጊዜ ጥቃት ተሰንዝሯል።

​እነዚህ ተቋማት 'በቱርክ ስትሪም' እና 'ብሉ ስትሪም' የጋዝ መስመሮች በኩል የሚደረገውን የውጭ ንግድ አቅርቦት አስተማማኝነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ኩባንያው አፅንዖት ሰጥቷል።

​ሁሉም ጥቃቶች መክሸፋቸው ተገልጿል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር፣ የዩክሬን ጦር ኃይሎች በጋዝፕሮም ተቋማት ላይ የሚሰነዝሩት ጥቃት ዓላማ ወደ አውሮፓ ደንበኞች የሚላከውን የጋዝ አቅርቦት ለማቋረጥ ነው ብሏል።

ከሩሲያ ወደ አውሮፓ የሚሄዱ ዋና ዋና የጋዝ መስመሮችን ለማየት ቪዲዮውን ይመልከቱ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0