የመጀመሪያ ደረጃ የምርመራ ውጤቶች በኢራን የሴቶች ትምህርት ቤት ለተፈጸመው ጥቃት አሜሪካ ተጠያቂ መሆኗን ያሳያሉ ተባለ
20:09 11.03.2026 (የተሻሻለ: 20:14 11.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የመጀመሪያ ደረጃ የምርመራ ውጤቶች በኢራን የሴቶች ትምህርት ቤት ለተፈጸመው ጥቃት አሜሪካ ተጠያቂ መሆኗን ያሳያሉ ተባለ
የካቲት 20 ቀን በኢራን ሚናብ ከተማ የሴቶች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በቶማሃውክ ሚሳኤሎች የተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት በአሜሪካ መፈጸሙን የወታደራዊ ምርመራ ማረጋገጡን ኒው ዮርክ ታይምስ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ፣ በአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ውስጥ የሚገኙ መኮንኖች ጥቃቱ የተፈጸመበትን ቦታ ነጥቦች ያዘጋጁት፣ በመከላከያ ደህንነት ኤጀንሲ በተሰጠ ጊዜው ያለፈበት መረጃ በመነሳት ነው።
ባለሥልጣናቱ እንደገለጹት፣ የምርመራው ውጤት አሁንም የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን፣ አሁን ያለው ዋናው ጥያቄ ለምን ጊዜው ያለፈበት መረጃ ሳይጣራ ለምን ጥቅም ላይ እንደዋለ ማወቅ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X