- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት እና የአፍሪካ አህጉራዊ የልማት አማራጮች

የመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት እና የአፍሪካ አህጉራዊ የልማት አማራጮች
ሰብስክራይብ
"በቅርቡ በኢራን የታዩትን ክስተቶች፣ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ በከፈቱት ጥቃት፣ እንዲሁም ትንሽ ቀደም ብሎ በቬንዙዌላ የሆነውን ስንመለከት፤ እነዚህ ክስተቶች ዓለም አቀፋዊውን መዋቅር እየቀየረ ያለ አዲስ ሥርዓት መኖሩን ይነግሩናል። አሁን ባለንበት ሁኔታም የኃይል ፖለቲካ ከሕግ የበላይነት በላይ እየገነነ መጥቷል። በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ያላደጉና በማደግ ላይ ያሉ አገራት ናቸው።" ሲሉ የልማት ኢኮኖሚስቱ እንዳልካቸው ስሜ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በመጀመሪያው ክፍል ከልማት ኢኮኖሚስቱ እንዳልካቸው ስሜ (ዶ/ር) ጋር በመሆን ዓለም አቀፋዊ የጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች—በተለይም በኢራን ዙሪያ ያለው አለመረጋጋት—በአፍሪካ የኢነርጂ ገበያ፣ የንግድ መስመሮች እና የኢኮኖሚ ስትራቴጂ ላይ ምን ተፅዕኖ ያሳድራሉ? የሚሉትን ጥያቄዎች የምንዳስስ ሲሆን፤ በክፍል ሁለት፦ የ2025 የዓለም አቀፍ የረሃብ መረጃ ጠቋሚ ግኝቶችን የአፍሪካ ህብረት ግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ጥበቃ ኮሚሽነር ከሆኑት ከሙሴ ቪላካቲ እና በኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ተመራማሪ ከሆኑት ደሳለኝ ቤኛ (ዶ/ር) ጋር ዳስሰነዋል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ :Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0