የአፍሪካ ሀገራት በቀድሞ ቅኝ ገዢዎች ለደረሰባቸው የባርነት ጥቃት ክስ ለመመስረት እያሰቡ መሆኑን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የአፍሪካ ሀገራት በቀድሞ ቅኝ ገዢዎች ለደረሰባቸው የባርነት ጥቃት ክስ ለመመስረት እያሰቡ መሆኑን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ
የአፍሪካ አገራት ለዘመናት ለተፈጸመባቸው የባርነት እና የኢምፔሪያሊዝም ተግባራት በቀድሞ የቅኝ ገዢዎች ላይ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ቅሬታቸውን ሊያቀርቡ እንደሚችሉ አንድ የእንግሊዝ ጋዜጣ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ዘገባው የትራንስ አትላንቲክ የባሪያ ንግድን በሰብአዊነት ላይ እንደተፈጸመ ወንጀል ሊቆጠር እንደሚገባም አመልክቷል።
ይህ ሊመሰረት የታሰበው ክስ ፈረንሳይን፣ ስፔንን፣ ፖርቹጋልን እና እንግሊዝን ኢላማ እንደሚያደርግ ዘገባው ጠቅሷል።
የአፍሪካ አገራት ይህንን የሕግ ስትራቴጂ የቀረጹት ሞሪሸስ ከበርካታ አስርት ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ እና ሕጋዊ ጥረት በኋላ የቻጎስ ደሴቶችን ለማስመለስ ካደረገችው ስኬታማ ተሞክሮ መነሳሳትን በመውሰድ እንደሆነ ተገልጿል።
የአፍሪካ ሕብረት በ39ኛው የመሪዎች ጉባኤው 'የባሪያ ንግድ' በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን አውጇል፡፡ አልጄሪያ የፈረንሳይን የቅኝ ግዛት ታሪክ በወንጀል ፈርጃለች፡፡ ጋና የባርያ ንድ ሰለባ ለሆኑ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትሕ መጠየቅን ዓላማው ያለው የውሳኔ ሐሳብ ለተባበሩት መንግሥታት የማቅረብ ዕቅድ ይዛለች፡፡
በሮተርዳም የሚገኝ የባርነት መታሰቢያ ሐውልት
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X