የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር "መጠነኛ" ያለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ
19:30 11.03.2026 (የተሻሻለ: 19:34 11.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር "መጠነኛ" ያለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ
ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው ይህ የዋጋ ጭማሪ፣ በየካቲት ወር በነበረው ዋጋ ላይ በሊትር፦
ነጭ ናፍጣ የ10 ብር፣
ነጭ ጋዝ የ7 ብር እና
ቤንዚን የ3 ብር ጭማሪ አለው።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ጦርነት የተነሳ የነዳጅ አቅርቦት ከፍተኛ መስተጓጎል እንደገጠመው ተናግረዋል።
አክለውም፣ ጦርነቱ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ስለማይታወቅ ሕብረተሰቡ እና ተቋማት ነዳጅን "በከፍተኛ ቁጠባ" እንዲጠቀሙ ያሳሰቡ ሲሆን መንግሥት በቅርቡ ተጨማሪ የነዳጅ ቁጠባ እርምጃዎችን ይፋ ያደርጋል ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X