የናይጄሪያው ዳንጎቴ በተጣሩ የነዳጅ ምርቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ
19:23 11.03.2026 (የተሻሻለ: 19:24 11.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የናይጄሪያው ዳንጎቴ በተጣሩ የነዳጅ ምርቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ
የኩባንያው ይፋዊ መግለጫ እንደሚያመለክተው፣ በቤንዚን እና በናፍታ የነዳጅ ምርቶቹ ላይ የዋጋ ቅናሽ ያደረገው በዓለም አቀፍ ደረጃ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ ምክንያት እንደሆነ ገልጿል።
የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ፣ ሰኞ ዕለት በአንድ በርሜል 119 ዶላር በላይ (ከጎርጎሮሳውያኑ ሰኔ 2022 ወዲህ ከፍተኛው ዋጋ) ደርሶ የነበረ ቢሆንም፣ ማክሰኞ ምሽት የቡድን ሰባት አባል አገራት የተጠራቀመ የነዳጅ ክምችት ሊለቀቅ እንደሚችል ከሰጡት መግለጫ በኋላ፣ ዋጋው በአንድ በርሜል 90 ዶላር በታች ወርዷል።
ቀደም ብሎ የዳንጎቴ ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ካለው ወቅታዊ ውጥረት መባባስ ጋር ተያይዞ ኩባንያቸው የናይጄሪያን የኃይል ዋስትና ለማረጋገጥ እንደሚሠራ ቃል ገብተው ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X