በምስራቅ ዲሞክራሲያ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙና የሰው ሕይወት መጥፋቱ ተዘገበ
19:13 11.03.2026 (የተሻሻለ: 19:14 11.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በምስራቅ ዲሞክራሲያ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙና የሰው ሕይወት መጥፋቱ ተዘገበ
የፈረንሳይ ዜና ወኪል የዐይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የድሮኖቹ ቁጥርና የደረሰው የጉዳት መጠን በዝርዝር አልታወቀም።
የሰሜን ኪቩ ክልል ዋና ከተማ ጎማ፣ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ነበር በኤም 23 አማጺያን ቁጥጥር ስር የወደቀችው። በዚህም ምክንያት የክልሉ መስተዳድር መቀመጫውን ወደ ቤኒ መቀየሩ ይታወሳል።
የኮንጎ ጦር ኃይሎች ሰሞኑን በአማጺያኑ ይዞታዎች ላይ የድሮን ጥቃቶችን ማጠናከራቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ከማኅበራዊ የትስስር ገፆች የተገኘ ቪዲዮ፣ የአማጺው ቡድን አዛዦች ይኖሩበት በነበረ ሕንፃ ላይ የደረሰውን የድሮን ጥቃት ውጤት እንደሚያሳይ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X