በአማራ ክልል ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ምገባ መረሃ ግብር ተጠቃሚ መሆናቸው ተዘገበ
18:18 11.03.2026 (የተሻሻለ: 18:24 11.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአማራ ክልል ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ምገባ መረሃ ግብር ተጠቃሚ መሆናቸው ተዘገበ
በክልሉ በሚገኙ ከ1 ሺህ 300 በላይ ትምህርት ቤቶች የምገባ መርሃ ግብር እየተከናወነ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን ወርቅነህ ለአገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ይህ ተነሳሽነት የተማሪዎችን የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ የትምህርትን ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ ያለመ መሆኑንና በክልሉ መንግሥት እና በሌሎች ደጋፊዎች በተመደበ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በጀት እንደሚንቀሳቀስ ተገልጿል።
መርሃ ግብሩ ሰብአዊነትን ማዕከል ባደረጉ ተግባራት ላይ ትኩረት ማድረጉ ተማሪዎች ከትምህርታቸው እንዳይርቁ እና የትምህርት ማቋረጥን ለመቀነስ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የቢሮው ሃላፊ ጥላሁን ወርቅነህ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን አሳውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X