ዓለም አቀፍ ቀውሶች የምግብ ዋስትና ስኬቶች እየፈተኑ ነው - ሪፖርት

ሰብስክራይብ

ዓለም አቀፍ ቀውሶች የምግብ ዋስትና ስኬቶች እየፈተኑ ነው - ሪፖርት

ከዚህ ቀደም ተገኝተው የነበሩ አበረታች ውጤቶች ከመቀዛቀዝ ባለፈ፣ አሁን ላይ ወደ ኋላ የመቀልበስ አደጋ እንደተደቀነባቸው በትናንትናው ዕለት በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ ይፋ የሆነው የ‘ግሎባል ሀንገር ኢንዴክስ 2025’ ሪፖርት ያሳያል፡፡

⏳ ሪፖርቱ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመቅረፍ የተያዘው ዕቅድ፣ አሳሳቢ በሆኑ ተግዳሮቶች ምክንያት በተቀመጠለት ጊዜ ላይሳካ እንደሚችል አመልክቷል።

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ፣ የዘንድሮው (2025) ውጤት ከዛሬ 10 ዓመት በፊት (2016) ከነበረው ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ መሻሻል የታየበት ቢሆንም፣ በቂ ለውጥ ግን አልተመዘገበበትም።

ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንዳንድ ሀገራት ፖሊሲ-ተኮር የሆኑ አበረታች ለውጦች መታየታቸውን ቢጠቅስም፤ በአፍሪካ ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራትና በደቡብ እስያ ግን ችግሩ አሁንም እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ስለመቀጠሉ ተመላክቷል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0