አፍሪካ ረሃብን ለማስወገድ ከራዕይ ወደ ተግባር መሸጋገር አለባት — የቀድሞ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

© telegram sputnik_ethiopiaአፍሪካ ረሃብን ለማስወገድ ከራዕይ ወደ ተግባር መሸጋገር አለባት — የቀድሞ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
አፍሪካ ረሃብን ለማስወገድ ከራዕይ ወደ ተግባር መሸጋገር አለባት — የቀድሞ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.03.2026
ሰብስክራይብ

አፍሪካ ረሃብን ለማስወገድ ከራዕይ ወደ ተግባር መሸጋገር አለባት — የቀድሞ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

የጎርጎሮሳውያኑ 2025 የዓለም ረሃብ መረጃ ጠቋሚ ይፋ በተደረገበት ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ደመቀ መኮንን፣ የአፍሪካ መሪዎች ረሃብን በመላው አኅጉሪቱ ለመቅረፍ ከፖሊሲ ማዕቀፎች ባለፈ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳሰቡ።

ረሃብ ተራ አኃዛዊ መረጃ ብቻ ሳይሆን፣ "የቀነጨረ ሕፃን" እና "የወደፊት ተስፋቸው በግጭትና በአየር ንብረት ለውጥ ስጋት ላይ የወደቀ ቤተሰብ" መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

አፍሪካ ከፍተኛ የተፈጥሮ ሀብት ያላት ቢሆንም፣ ዋናው እንቅፋት የሥርዓት መውደቅ መሆኑን በንግግራቸው ጠቁመዋል፡፡

የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚከትሉት እርምጃዎች እንዲወሰዱ አሳስበዋል።

▪ የተፈጥሮ ሀብትን ከምግብ ምርት ጋር የሚያገናኙ ጠንካራ ትስስሮች እንዲፈጠሩ፤

▪ ለአየር ንብረት እና ለኢኮኖሚ ቀውሶች የማይበገሩ ኢንቨስትመንቶች እንዲጨምሩ

▪ሴቶችን እና ወጣቶችን የሚያበረታቱ የግብርና ሥርዓቶች እንዲዘረጉ እንዲሁም

▪በዓለም አቀፍ እና በአገር በቀል ተዋንያን መካከል ጠንካራ ትብብር እንዲኖር፡፡

ደመቀ መኮንን፣ መንግሥታት የምግብ ዋስትናን እንደ ዋና የብሔራዊ ልማት ግብ እንዲያስቀድሙ ማሳሰባቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0