- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
Continental Drift' በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የአለም የደቡብን ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚከታተል ፕሮግራም ነው።ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

መካከለኛው ምስራቅ ቀዉስ ፦ የዓለም አቀፍ የሕግና ሥርዓት ዕጣ ፈንታ ነጋሪ ?

መካከለኛው ምስራቅ ፦ የዓለም አቀፍ የሕግና ሥርዓት ዕጣ ፈንታ ነጋሪ
ሰብስክራይብ
በመካከለኛው ምስራቅ እየታየ ያለው ቀውስ የአንድ ቀጠና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ የተመሰረተው ዓለም አቀፍ የሕግ ሥርዓት ታላቅ ፈተና ነው። በኢራን ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እና እየተባባሰ የመጣው ውጥረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተርን እና የሉዓላዊነት መርሆዎችን አደጋ ላይ ጥሏቸዋል።
"ሩሲያና ቻይና ሁነቶቹን በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውና ከትዕይንቱ በስተጀርባ የራሳቸውን ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው በጣም ግልጽ ነው። ከሚታየው ነገር ባሻገር ጠልቀን ማየት አለብን። በአንድ በኩል በዩናይትድ ስቴትስና በእስራኤል፣ በሌላ በኩል ደግሞ በኢራን መካከል በመካከለኛው ምስራቅ እየተከሰተ ባለው የፖለቲካ ቀውስ ቻይና እና ሩሲያ በዝምታ ተቀምጠዋል ብዬ አላስብም፤ ምክንያቱም ይህ ቀጠና ለዓለም አቀፍ ፖለቲካ በጣም ስሜታዊ ስፍራ ነው።" ሲሉ አብዱ መሐመድ (ዶ/ር) ፣ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረትን እና የዓለም አቀፍ ሕግጋት መሸርሸርን በተመለከተ ከሁለት ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያዎች — አብዱ መሐመድ (ዶ/ር) የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ እና ከዳዊት መዝገበ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ጋር በጥልቀት እንወያያለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0