የአእምሮ እስር ሲሰበር፦ ሁለተኛ ዲግሪውን በማዕረግ ያጠናቀቀው የእድሜ ልክ ፍርደኛ

© telegram sputnik_ethiopiaየአእምሮ እስር ሲሰበር፦ ሁለተኛ ዲግሪውን በማዕረግ ያጠናቀቀው የእድሜ ልክ ፍርደኛ
የአእምሮ እስር ሲሰበር፦ ሁለተኛ ዲግሪውን በማዕረግ ያጠናቀቀው የእድሜ ልክ ፍርደኛ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.03.2026
ሰብስክራይብ

የአእምሮ እስር ሲሰበር፦ ሁለተኛ ዲግሪውን በማዕረግ ያጠናቀቀው የእድሜ ልክ ፍርደኛ

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በዝዋይ ማረሚያ ቤት በእርምት ላይ የሚገኘው አበባየሁ ሳሙኤል፣ 12 ዓመታት የእርምት ጊዜ አሳልፏል፡፡ በማረሚያ ቤቱ ቆይታው ውስጥ 3 ዓመት ከ5 ወራቱን “ያለአግባብ” ማሳለፉን ገልጿል፡፡

ቢዘገይም፣ የሰብአዊ መብት የሆነውን የመማር እና አዕምሮን የመጠቀም መብት ወደ ተግባር በመቀየር ትምህርት መጀመሩን ያስታውሳል፡፡ ጅማሮውን አጠናክሮ በማስቀጠል የሁለት ዲግሪዎች ባለቤት ለመሆን በቃ፡፡

በሥነ–መለኮት ትምህርት በከፍተኛ ማዕረግ የመጀመሪያ ዲግሪውን እና በሊደርሺፕ ማኔጅመንት በከፍተኛ ውጤት ሁለተኛ ዲግሪውን መያዙን ማረሚያ ቤቱ አስታውቋል።

የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ የትምህርት ሞጅሎች እንዲያገኝ በማገዝና መምህራን ማረሚያ ቤት ድረስ እየመጡ ቱቶሪያሎችን እንዲሰጡት በማድረግ ላስመዘገበው ውጤት ማረሚያ ቤቱ ትልቅ አስታዋፆ እንዳለው መስክሯል ሲል የፌድራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የአእምሮ እስር ሲሰበር፦ ሁለተኛ ዲግሪውን በማዕረግ ያጠናቀቀው የእድሜ ልክ ፍርደኛ - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የአእምሮ እስር ሲሰበር፦ ሁለተኛ ዲግሪውን በማዕረግ ያጠናቀቀው የእድሜ ልክ ፍርደኛ - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የአእምሮ እስር ሲሰበር፦ ሁለተኛ ዲግሪውን በማዕረግ ያጠናቀቀው የእድሜ ልክ ፍርደኛ - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0