በአዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ የአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርትን ከሦስት ወደ አሥር በመቶ ለማሳደግ መታቀዱ ተገለጸ
16:21 10.03.2026 (የተሻሻለ: 16:24 10.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ የአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርትን ከሦስት ወደ አሥር በመቶ ለማሳደግ መታቀዱ ተገለጸ
ፖሊሲው በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውንና አማራጭ የሆነውን ኮንፈረንስ ቱሪዝምን ማስተዳደር የሚያስችል ራሱን የቻለ ተቋም ማቋቋም ያስችላል ተብሏል።
ይህ ከ17 ዓመታት በኋላ ባለፈው ሳምንት የፀደቀው ሁለተኛው የቱሪዝም ፖሊሲ፣ በቀድሞ ፖሊሲ ውስጥ ትኩረት ላልተሰጣቸው የአገር ውስጥ ቱሪዝም፣ የኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን ቱሪዝም አማራጮች ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያን በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻ የማድረግ ዓላማ አለው ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዲኤታው፣ ባለፈው ዓመት ከ150 በላይ ኮንፈረንሶች በኢትዮጵያ መካሄዳቸውን፣ ዘንድሮም በርካታ ዕድሎች እየመጡ በመሆናቸው በሕግና በሥርዓት መመራት እንደሚኖርበት ለአገር ውስጥ የግል ሚዲያ ገልፀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X