በሦስተኛው የዓለም ጦርነት የመጀመሪያ ቀናት ላይ ሳንሆን አይቀርም - የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ጄፍሪ ሳክስ

ሰብስክራይብ

በሦስተኛው የዓለም ጦርነት የመጀመሪያ ቀናት ላይ ሳንሆን አይቀርም - የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ጄፍሪ ሳክስ

ሳክስ፣ ባለፈው ዓመት መጋቢት መጨረሻ ላይ፣ በጎርጎሮሳዊያኑ 2001 የወጣውንና “በአምስት ዓመታት ውስጥ ሰባት ጦርነቶች” የሚል ዝርዝር የያዘ የፔንታጎን ምስጢራዊ ሰነድ ጠቅሰዋል። በዚህም ዋሽንግተን እና ቴል አቪቭ፦ በሶሪያ፣ ሊባኖስ፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ውስጥ ለተቀሰቀሱ ግጭቶች ተጠያቂ መሆናቸውን አመልክተዋል።

​በወቅቱ በዝርዝሩ ላይ ከሰፈሩት ውስጥ ያልተካሄደው ብቸኛው ጦርነት በኢራን ላይ የሚደረገው ብቻ እንደነበር የገለጹት ሳክስ፤ ዛሬ ላይ ግን ትንበያቸው እውን እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።

የአሜሪካ ስትራቴጂ አንዱ አካል የኃይል ገበያውን መቆጣጠር እና ማጥበብ ይመስላል” ሲሉ አፅንኦት የሰጡት ሳክስ፣ በአሁኑ ወቅት ይህ ጥረት በየሰዓቱ የኃይል አቅርቦትን እያስተጓጎለ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ላይ በዩክሬን እና በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄዱ የሚገኙ ግጭቶች በተመሳሳይ ጊዜ እየተካሄዱ መሆኑንና በፓኪስታን እና አፍጋኒስታን መካከልም ውጥረት እየነገሰ መሆኑንም የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አክለው ጠቅሰዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0