ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሐረሪ ክልል የተተገበረውን የገጠር ኮሪደር ሥራ አወደሱ

ሰብስክራይብ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሐረሪ ክልል የተተገበረውን የገጠር ኮሪደር ሥራ አወደሱ

በክልሉ ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ ውስጥ የተሠራው የገጠር ኮሪደር ሥራ በአካባቢው በተገኙ ቁሳቁሶች፤ በኅብረተሰብ ተሳትፎ የተከናወነ የአነስተኛ መንደር ሞዴል ክንውን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“የአካባቢው ነዋሪ በንቃት የተሳተፈበት የገጠር ኮሪደር ሥራ ባሕላዊ የግንባታ ዘዴን፣ የተደራጀ እቅድ እና ተግባራዊ የአሠራር ውጤት ያሳየ ነው።” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል፡፡

ዐቢይ በሐረሪ ክልል እና በሐረር ከተማ ጉብኝታቸው፦

የዱር ፈረሶችና ዋሻዎች የሚገኙባቸውን የቁንድዶ ተራሮች ተመልክተዋል፡፡

8 ተቋማት በ24 መስኮቶች 67 የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡበትን የሐረር ከተማ የመሶብ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

ከሐረር ከተማ ነዋሪዎች ጋር የረመዳን ኢፍጣር ተጋርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረሪ ክልል ያደረጉትን ጉብኝት ከቪዲዮው ይመልከቱ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0