የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በፋርስ ባህረ ሰላጤ እየተባባሰ ስላለው ውጥረት ስጋቱን ገለጸ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በፋርስ ባህረ ሰላጤ እየተባባሰ ስላለው ውጥረት ስጋቱን ገለጸ
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በፋርስ ባህረ ሰላጤ እየተባባሰ ስላለው ውጥረት ስጋቱን ገለጸ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.03.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በፋርስ ባህረ ሰላጤ እየተባባሰ ስላለው ውጥረት ስጋቱን ገለጸ

​የኃይል እና የትራንስፖርት ተቋማትን ጨምሮ በዋና ዋና መሰረተ ልማቶች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ወሳኝ የሆኑ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን እያስተጓጎሉ መሆናቸውንና ይህም በዓለም አቀፍ የንግድ እና የኃይል ገበያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ገልጸዋል።

​ ሊቀመንበሩ ዓለም አቀፍ ሕግጋትን የሚጥሱ እና የሀገራትን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን የኮነኑ ሲሆን፣ ሁሉም ወገኖች ራሳቸውን እንዲገቱ አሳስበዋል። ውጥረቶችን ለመቀነስ እና ተጨማሪ ግጭቶችን ለመከላከል አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች እንዲደረጉም ጥሪ አቅርበዋል።

በባህረ ሰላጤው አካባቢ ያለው መረጋጋት ለዓለም አቀፍ የኃይል ደህንነት እና ለዓለም ኢኮኖሚ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት የሰጡት ዩሱፍ፣ ይህም በአፍሪካ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እንዳለው ጠቁመዋል።

የነዳጅ ዋጋ መጨመር፣ የንግድ መስመሮች መቋረጥ እና ሊበላሹ የሚችሉ ሸቀጦችን ወደ ውጭ ለመላክ የሚገጥሙ ተግዳሮቶች በገበያው ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

​ የአፍሪካ ሕብረት ለዓለም አቀፍ ሕግጋት እና ለሰላማዊ መፍትሄ ውይይቶች ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጡት ሊቀመንበሩ፣ ኮሚሽኑ በአካባቢው ያሉትን ሁኔታዎች በቅርበት መከታተሉን እንደሚቀጥልም አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0