የነዳጅ ዋጋ መናር ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል - ባለሙያ
10:51 10.03.2026 (የተሻሻለ: 10:54 10.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የነዳጅ ዋጋ መናር ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል - ባለሙያ
የነዳጅ ዋጋ በአንድ በርሜል ከ100 ዶላር በላይ መሆኑ “በትራንስፖርት፣ በሎጂስቲክስ እና በንግድ ወጪዎች አማካኝነት በሸማቾች ዋጋ ላይ ጫና ይፈጥራል” ሲሉ ሩሲያዊው ባለሙያ አሌክሲ ፕሪማክ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
“ይህ የዋጋ ደረጃ ለተከታታይ ወራት ከቀጠለ፣ ማዕከላዊ ባንኮች ገበያው ከሚጠብቀው በላይ ለረጅም ጊዜ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲን ለመከተል ይገደዳሉ። ይህም ለዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ መቀዝቀዝ ስጋትን ይጨምራል” ሲሉ ፕሪማክ ጠቁመዋል።
ባለሙያው አክለውም፣ በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ስር የሰደደ መዘዝ ሊከሰት የሚችለው የነዳጅ ዋጋ ከ115 ዶላር በላይ ሆኖ ለረጅም ጊዜ ከቀጠለና ከአቅርቦት መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ከመጣ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል።
“ለአሁኑ ገበያው ሁኔታውን እንደ ስጋት እንጂ እንደማይቀር ቀውስ አድርጎ አልተመለከተውም” ሲሉ ባለሙያው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መለኪያ የሆነው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ፣ ከጎርጎሮሳውያኑ ሰኔ 2022 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በ29 በመቶ በመጨመር በአንድ በርሜል ከ119 ዶላር በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X