ዓለም አቀፍ የብዝኃ-ዋልታ ሥርዓት በአሜሪካ እና እስራኤል የኢራን ጥቃት ወቅት ውጥረት ውስጥ ገብቷል
10:12 10.03.2026 (የተሻሻለ: 11:09 10.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ባለብዙ ወገን የትብብር ሥርዓት እየፈራረሰ ነው - ተንታኝ
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸሙት የቅርብ ጊዜ ጥቃቶች ባለብዙ ወገን የትብብር ሥርዓት እየተዳከመ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን በአፍሪካ ቀንድ እና በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት ተመራማሪ እና ተንታኝ ራሺድ አብዲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ተንታኙ እንዳሉት፣ እነዚህ ድርጊቶች በሚፈጽሟቸው አካላት ዘንድ ፖለቲካዊ ምክንያት ሊኖራቸው ቢችልም፣ በዓለም አቀፍ ሕግ መነጽር ሲታዩ ግን ለመከላከል አዳጋች ናቸው።
በግጭቱ ተሳታፊ አካላት መካከል ለዲፕሎማሲያዊ ድርድር በቂ ጊዜ አለመሰጡትን በአፅንኦት የተናገሩት ረሺድ፣ አሁን ላይ ትኩረት መደረግ ያለበት ውጥረትን ወደ ማርገብ እና ድርድሮችን እንደገና ወደ ማስጀመር ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። ኢራን በክልሉ ግዙፍ ኃይል እንደመሆኗ፣ የመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋት ከአፍሪካ መረጋጋት ጋር በቅርበት የተሳሰረ መሆኑን አስረድተዋል።
እንደ ረሺድ ገለጻ፣ ይህ ቀውስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መጠነ-ሰፊ ፈተናን የፈጠረ ሲሆን፣ ይህም ኃያላን መንግሥታት የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን አልፈው እንዳይሄዱ መከላከል ነው።
"የተባበሩት መንግሥታት ሥርዓት፣ ዓለምን ለማረጋጋት በእጃችን ያለው ብቸኛው መሣሪያ ነው" ብለዋል ተንታኙ። አክለውም፣ ውይይትን ወደነበረበት ለመመለስ እና ውጥረትን ለመቀነስ በዓለም አቀፍ እና በክልል አቀፍ ተዋንያን መካከል ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X