በኢራን-እስራኤል ግጭት ምክንያት የኬንያ የስጋ ላኪዎች 7.3 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ከፍተኛ ኪሳራ አጋጠማቸው
20:05 09.03.2026 (የተሻሻለ: 20:14 09.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢራን-እስራኤል ግጭት ምክንያት የኬንያ የስጋ ላኪዎች 7.3 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ከፍተኛ ኪሳራ አጋጠማቸው
ወደ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ኦማን እና ኩዌት እንዲላኩ ታቅደው የነበሩ ከ200 ቶን በላይ የበሬ እና የፍየል ስጋዎች በአሁኑ ወቅት በኬንያ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ማቀዝቀዣዎች ውስጥ ተከማችተው ይገኛሉ።
የኬንያ የስጋ እና የእንስሳት ላኪዎች ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኒኮለስ ንጋሁ እንደገለፁት፤ የበረራዎች መሰረዝ እና የጉዞ መስመር መቀየር አውሮፕላኖች ወደ ኬንያ እንዲመለሱ በማድረጉ የሎጂስቲክስ ችግሩ ተባብሷል፤ በተጨማሪም የካርጎ አቅም መገደብ የትራንስፖርት ወጪን በእጅጉ እንዲጨምር አድርጓል።
የ"ትሪፕል ዘ ኢምፓክት ሴንተር ኦፍ ገቨርናንስ ኤንድ ፓብሊክ ኢንጌጅመንት" ዋና ስራ አስፈፃሚ ጃዋሬ ጄኤም በበኩላቸው፣ ግጭቱ የሚቀጥል ከሆነ ኬንያ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ሊደርስባት እንደሚችል ተናግረዋል።
"ጦርነቱ የሚቀጥል ከሆነ በኢኮኖሚው በርካታ ዘርፎች ላይ ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድሉ ከፍተኛ ነው" ሲሉ ጃዋሬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ሪዳህ ቼቤት ያዘጋጀችውን ሙሉ ዘገባ ከላይ ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X