በኢትዮጵያ 30 ሚሊዮን ሴቶችን የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ ያለመ ንቅናቄ ተጀመረ
17:34 09.03.2026 (የተሻሻለ: 17:44 09.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ 30 ሚሊዮን ሴቶችን የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ ያለመ ንቅናቄ ተጀመረ
የሴቶች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ ዓላማም በመጪው ሰኔ ወር እንደሀገር አጠቃላይ የተመዝጋቢዎችን ቁጥር 90 ሚሊዮን ለማድረስ የተያዘውን ግብ ለማሳካት መሆኑን ተገልጿል።
🪪 የሴቶች ፋይዳ መታወቂያ ምዝገባና ብሔራዊ የምዝገባ መርሃግብር የማይነጣጠሉ እንደሆነ የገለጹት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ ዮዳሔ አርአያሥላሴ፣ እስካሁን ድረስ የፋይዳ መታወቂያ ተመዝጋቢ ዜጎች ቁጥር 37 ሚሊዮን መድረሱን አክለዋል።
ከአጠቃላይ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 60 በመቶ ወንዶችና ቀሪዎቹ ሴቶች መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X