'ዓለም አቀፍ ሕግ ከዚህ በኋላ ፋይዳ የለውም' - ኢትዮጵያዊ ምሁር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ'ዓለም አቀፍ ሕግ ከዚህ በኋላ ፋይዳ የለውም' - ኢትዮጵያዊ ምሁር
'ዓለም አቀፍ ሕግ ከዚህ በኋላ ፋይዳ የለውም' - ኢትዮጵያዊ ምሁር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.03.2026
ሰብስክራይብ

'ዓለም አቀፍ ሕግ ከዚህ በኋላ ፋይዳ የለውም' - ኢትዮጵያዊ ምሁር

አሜሪካ ከቴህራን ጋር ያካሄደችው ድርድር የይምሰልና ኢራን ላይ ከወጠነችው ወታደራዊ ጥቃት በፊት ጊዜ የገዛችበት ስትራቴጂ ነበር ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ እና የኢኮኖሚ ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"[ይህ] የኢራን ሕዝብ የማይፈልገው የስርዓት ለውጥ ነው። በዘላቂነት ምን እንደሚያስከትል አላውቅም" ሲሉ አክለዋል።

በእነዚህ ክስተቶች መካከል የተባበሩት መንግሥታት በመሥራች አባላቶቹ ተሸርሽሮ "ጣረ ሞቱ ላይ ነው" ሲሉ ምሁሩ አፅንዖት ሰጥተዋል።

ስፔን ጦርነቱ ሕገ-ወጥ ነው በማለት የያዘችውን ግልፅ አቋም ያነሱት ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር)፤ ትራምፕ ከማድሪድ ጋር ያለውን የንግድ ግንኙነት እንደሚያቋርጡ ማስፈራራታቸው፤ አሜሪካ የምትለውን ለማይቀበል ማንኛውም ሀገር ማስጠንቀቂያ መሆኑ ነው ብለዋል።

"በንፅፅር አፍጋኒስታን እና ቬትናም የፌዝ ሊመስሉ ይችላሉ፤ ምክንያቱም ይህ የመካከለኛው ምስራቅ ዕምብርት ነው።"

እንደ ምሁሩ ገለጻ፤ ለሰላም ብቸኛው መንገድ ዋሽንግተን ለእስራኤል የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም የሚያስገድድ በባሕረ ሰላጤው ሀገራት ዙሪያ የሚፈጠር መሠረታዊ ለውጥ ብቻ ነው።

እስከዚያው ድረስ ግን ኢራን ግዛቷንና አገዛዟን እየተከላከለች ጸንታ ትቆማለች ሲሉ ምሁሩ ደምድመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0