የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የአፍሪካ ሀገረ ስብከት በናይጄሪያ ጥቃት ለደረሰባቸው ክርስቲያኖች የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ጀመረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የአፍሪካ ሀገረ ስብከት በናይጄሪያ ጥቃት ለደረሰባቸው ክርስቲያኖች የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ጀመረ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የአፍሪካ ሀገረ ስብከት በናይጄሪያ ጥቃት ለደረሰባቸው ክርስቲያኖች የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.03.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የአፍሪካ ሀገረ ስብከት በናይጄሪያ ጥቃት ለደረሰባቸው ክርስቲያኖች የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ጀመረ

በናይጄሪያ ቤኑዌ ግዛት ቱራን በተሰኘ የክርስቲያን መንደር ላይ እስላማዊ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 10 የሚደርሱ ሰዎች ተገድለዋል። እንደ ሞስኮ ፓትርያርክ መግለጫ ከሆነ፤ እርዳታው ለሟች ቤተሰቦች እና ቤታቸውንና መተዳደሪያቸውን ላጡ የመንደሩ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ይውላል።

የማኅበረሰቡ አስተዳዳሪ ቄስ ኒፎንት እንደተናገሩት፤ ሰዎች ሁሉንም ነገር ጥለው ለመውጣት እንደተገደዱ እና ተፈናቃዮች ወደ አቅራቢያው ከተማ በብዛት በመጉረፋቸው የመጠጥ ውሃ እና ምግብ ማግኘት እንኳን አስቸጋሪ ሆኗል። አንዳንዶቹም የሕክምና እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

እስካሁን መጀመሪያ ከታቀደው 25 ሺህ ዶላር በላይ 31,540 ዶላር ተሰብስቧል።

ቀደም ሲል በናይጄሪያ ቤኑዌ ግዛት ቱራን መንደር አሸባሪዎች ሁለት የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን አባላትን ጨምሮ ቢያንስ አሥር ክርስቲያኖችን ገድለዋል። ባለሥልጣናት በአካባቢው ፍለጋቸውን ሲቀጥሉ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል። በመንደሩ 20 ሕፃናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 50 ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ይኖሩ ነበር ተብሏል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0