ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ሳቢያ ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሥጋ ምርት መላክ አቆመች
17:46 08.03.2026 (የተሻሻለ: 17:54 08.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ሳቢያ ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሥጋ ምርት መላክ አቆመች
አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት በመካከለኛው ምስራቅ የበረራ መስተጓጎል በመፍጠሩ ወደ ዱባይ የሚላከው የሥጋ ምርት ሙሉ በመሉ ተቋርጦ ወደ ሳዑዲ አረቢያ መዛወሩን የሥጋ አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር ኃላፊ ነግረውኛል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ሀገሪቱ 30 በመቶ የኢትዮጵያ ስጋ ምርት መዳረሻ እንደነበረች ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደማም የሚያደርገውን በረራ ቢያቋርጥም በጅዳ እና ሪያድ የሚያደርገውን በረራ እንዲጨምር በማድረግ የሥጋ ምርቱ ወደ ሳዑዲ አረቢያ እየተላከ ነው ተብሏል።
የገበያ ዝውውሩ ወቅቱ የረመዳን ጾም ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሳዑዲ አረቢያ የሥጋ ፍላጎት ከፍተኛ መሆኑ የተፈጠረውን የገበያ ክፍተት ለማጥበብ ማስቻሉም ተጠቁሟል።
የሳዑዲ ገበያ ላይ ችግር ቢፈጠር ምርቱን በእስያ በቻይና ሆንግ ኮንግ እና ቬትናም፤ አፍሪካ ውስጥ ደግሞ የጊኒ እና ሲሸልስ ገበያዎች ምልከታ እየተደረገባቸው እንደሆነ ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X