የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሀገራዊ የኃይል ምርት ድርሻ 51 በመቶ ደረሰ
15:38 08.03.2026 (የተሻሻለ: 15:44 08.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሀገራዊ የኃይል ምርት ድርሻ 51 በመቶ ደረሰ
ይህ የተነገረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸሙን ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ባቀረበበት ወቅት ነው።
ግድቡ ግንባታው ተጠናቆ ሥራ መጀመሩን ተከትሎ ሀገራዊ የኃይል ምርት በ36 በመቶ እንዲያድግ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ተጫውቷል ተብሏል።
በተጠቀሰው ጊዜ 20.3 ቴራ ዋት ሰዓት ኃይል ለማምረት ታቅዶ 18.3 ቴራ ዋት ሰዓት ኃይል ማሳካት ተችሏል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከጎረቤት ሀገራት የኃይል ሽያጭ እና ዳታ ማይኒንግ 247.7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘም አስታውቋል።
ተቋሙ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በበጀት ዓመቱ አካፋይ 7.1 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዝግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X