ታንዛኒያዊው ዲፕሎማት የምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ዋና ፀሐፊ በመሆን ኃላፊነት ተረከቡ
14:46 08.03.2026 (የተሻሻለ: 14:54 08.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ታንዛኒያዊው ዲፕሎማት የምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ዋና ፀሐፊ በመሆን ኃላፊነት ተረከቡ
አምባሳደር ስቴፈን እምቡንዲ፤ ቬሮኒካ ንዱቫን በመተካት ከ2026 እስከ 2031 ለማገልገል በአባል ሀገራት መሪዎች ፊት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
ከ28 ዓመታት በላይ የሥራ ልምድ ያላቸው አንጋፋው ዲፕሎማት፤ ቀደም ሲል በታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ እና የምስራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስቴር ውስጥ በቋሚ ፀሐፊነት አገልግለዋል።
የታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ እና የምስራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ እምቡንዲ ቀጣናዊ ውህደትን ለማሳደግ ከምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ተቋማት፣ ከልማት አጋሮች እና ከግል ባለድርሻ አካላት ጋር ለረጅም ጊዜ በጋራ ሠርተዋል።
ሹመቱ የጥምረቱን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ትብብር ጥረቶች ይበልጥ ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X