"ዓድዋ የኢትዮጵያውያን ዘመን ተሻጋሪ ድልና የወል ትውስታ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ
14:18 08.03.2026 (የተሻሻለ: 14:24 08.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"ዓድዋ የኢትዮጵያውያን ዘመን ተሻጋሪ ድልና የወል ትውስታ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ
የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሂዷል።
በደራሲ አሻግሬ ገብረወልድ (ዶ/ር) የተጻፈው ይህ መጽሐፍ፤ በ26 ምዕራፎች የተከፈለና ከ1 ሺህ በላይ ገጾችን የያዘ ግዙፍ የታሪክ ድርሳን ነው ተብሏል።
በወቅቱ ንግግር ያደረጉት የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር "ዋጋ የከፈሉትን ፋኖስ እንድናደርጋቸው የሚያግዝ ነው። ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን በደንብ በመግለጽ ዓድዋን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲረዳው ማድረግም ሌላው የመጽሐፉ አስተዋጽዖ ነው" ብለዋል።
የታሪክ ድሉን ብርታትና የአባቶችን ጽናት ከመዘከር ባለፈ፤ ታሪክ የዘነጋቸውን ጀግኖች ለማስታወስና ትናንትን ከዛሬ ጋር ለማገናኘት ታቅዶ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
መጽሐፉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪነት እንደተዘጋጀ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X