የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2026 ከአፍሪካ ግዙፉ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ተብሎ ተመረጠ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2026 ከአፍሪካ ግዙፉ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ተብሎ ተመረጠ

የአፍሪካ የጉዞ እና የቱሪዝም ማኅበር ባወጣው አዲስ ሪፖርት፤ አየር መንገዱ በዓመቱ የመጀመሪያዎቹ አስር ወራት ውስጥ ብቻ 23.8 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ ይፋ አድርጓል።

ይህም በ2024 ካስተናገደው 20.9 ሚሊዮን መንገደኞች አንጻር ከፍተኛ ዕድገት የተመዘገበበት እንደሆነ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ተከትለው ኢጂፕት ኤር፣ ሳፋኤር፣ ሮያል ኤር ማሮክ እና ኤር አልጄሪ ከአኅጉሪቱ ቀዳሚ አምስት አየር መንገዶች ዝርዝር ውስጥ ተቀምጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0