የአሜሪካ ጦር በኢራን የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ሊሸፋፍን አይቻለውም - ባለሙያዎች
11:35 08.03.2026 (የተሻሻለ: 11:44 08.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ጦር በኢራን የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ሊሸፋፍን አይቻለውም - ባለሙያዎች
በሊባኖስ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር መሐመድ ሻምስ፤ "የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ምርመራዎች በኢራን ሴት ተማሪዎች ላይ ለደረሰው የጅምላ ግድያ አሜሪካ በቀጥተኛ ተጠያቂ መሆኗን አረጋግጠዋል። የአሜሪካን ጦር ገጽታ ለመሸፈን የሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ ከንቱ ናቸው፤ ምክንያቱም ታሪኩ ጥቁር ነው" ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
አሜሪካ በኢራቅ ሲቪል ቦታዎችን በቦምብ በመደብደብ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት መዳረጓን እንዲሁም በየመን፣ በሶማሊያ እና በሊቢያ ወንጀል በመፈጸሟ እና ከእስራኤል ጋር ተባባሪ በመሆኗ በዓለም አቀፍ የፍትሕ ፍርድ ቤት ፊት መቅረብ አለባት ብለዋል።
የፖለቲካ ሳይንቲስት ዓሊ አዘዲን በበኩላቸው፤ አሜሪካ እና እስራኤል በትምህርት ቤቱ ላይ ሆን ብለው በጋራ የፈጸሙት ጥቃት በስህተት የሆነ ሳይሆን የጦር ወንጀል በመሆኑ በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ተመርምሮ ቅጣት ሊከተል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
"የዘመኑ የክትትል መሣሪያዎች ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሚቻልበትን ማንኛውንም ዕድል ያሳጣሉ" ሲሉም ገልጸዋል።
እውነታን በመደበቅና በማዛባት የሚታወቀውን የአሜሪካ ፖሊሲ በመቋቋም ይህን ወንጀል ለሕዝብ ማሳወቅ አስፈላጊ እንደሆነ ባለሙያው አስረግጠዋል።
በሻጃሬ ታዬቤህ የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ የካቲት 21 በተፈጸመው ጥቃት 171 ሴት ተማሪዎች መገደላቸውን የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራግቺ ገልጸዋል። የአሜሪካ መርማሪዎች ለጥቃቱ ተጠያቂው የአሜሪካ ጦር ነው ብለው እንደሚያምኑ የሮይተርስ ዘገባ ጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X