የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በማስመልከት በ8 ሀገራት በሴቶች ብቻ የሚመራ በረራ እንደሚያደርግ አስታወቀ
19:02 07.03.2026 (የተሻሻለ: 19:14 07.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በማስመልከት በ8 ሀገራት በሴቶች ብቻ የሚመራ በረራ እንደሚያደርግ አስታወቀ
ከነገ ጀምሮ ወደ ካይሮ፣ ጅቡቲ፣ ናይሮቢ፣ ፍራንክፈርት፣ አክራ፣ ሙምባይ፣ ዊንድሆክ እና ድሬዳዋ በድምሩ 8 በረራዎች እንደሚደረጉ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
በረራው ሴቶች አብራሪነትን ጨምሮ በሁሉም የአቪዬሽን ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳየት በማሰብ የሚከናወን መሆኑንም ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው የአየር መንገዱ የሴት አብራሪዎች ቁጥር 95 መድረሱን ገልጸዋል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
አየር መንገዱ የሴቶችን ቀን በማስመልከት ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ በሴቶች ብቻ የሚመራ በረራ ሲያደርግ ቆይቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/3
© telegram sputnik_ethiopia

2/3
© telegram sputnik_ethiopia

3/3
© telegram sputnik_ethiopia
1/3
© telegram sputnik_ethiopia
2/3
© telegram sputnik_ethiopia
3/3
© telegram sputnik_ethiopia