የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ ግድያ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲን ወደ ግድያ ፖለቲካ ሊለውጥ ይችላል - የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ ግድያ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲን ወደ ግድያ ፖለቲካ ሊለውጥ ይችላል - የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ
የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ ግድያ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲን ወደ ግድያ ፖለቲካ ሊለውጥ ይችላል - የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.03.2026
ሰብስክራይብ

የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ ግድያ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲን ወደ ግድያ ፖለቲካ ሊለውጥ ይችላል - የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ

የአንድን ሀገሪ መሪ መግደል የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን የሚጥስ ነው የሚሉት ተንታኙ ሞሃመድ ሲራጅ፤ የካሜኒ ግድያ እ.አ.አ በ1973 የወጣውን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጠበቁ ሰዎች ኮንቬንሽንን የጣሰ ወንጀል እንደሆነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

“ከአያቶላው ጋር ተያይዞ በኢራን ላይ የተወሰደው እርምጃ የዓለም አቀፍ ሕግና ሉዓላዊነትን እንዲሁም በሕዝብ ይሁንታ የተመረጠን ወይም የተቀመጠን የመንግሥት መሪን በመግደል የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር አንቀጽ ሁለት ንዑስ አንቀጽ አራትን የሚጥስ ሆኖ እናገኘዋለን።”

ድርድር ለወታደራዊ ዝግጅት ሽፋን የሆነበት መንገድ ደግሞ ሀገራት ከጠረጴዛ ይልቅ ጦርን እንዲያስቀደሙ የሚገፋፋና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ላይ ዕምነት የሚያሳጣ አካሄድ እንደሆነም አክለዋል፡፡

“ይሄ ድርጊት በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ ትልቁን ካፒታል ‘መተማመንን’ የሚያሳጣ ነው፡፡...ሀገራት በጠረጴዛ ዙሪያ ከሚደረግ ስምምነት ይልቅ ወታደራዊ ዝግጅትን ብቸኛ አማራጭ አድርገው እንዲወስዱ ሊገፋፋቸው ይችላል።”

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0