በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የኤአይ ሙዚቃ ውድድር ሊካሄድ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የኤአይ ሙዚቃ ውድድር ሊካሄድ ነው
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የኤአይ ሙዚቃ ውድድር ሊካሄድ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.03.2026
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የኤአይ ሙዚቃ ውድድር ሊካሄድ ነው

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከእሁድ ኤ.አይ ስቱዲዮ ጋር በመተባበር በአጠቃላይ አንድ ሚሊዮን ብር የሚያሸልም የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የሙዚቃ ውድድር ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

የኢትዮጵያን ባሕል፣ ታሪክ እና እሴቶችን የሚገልፁ እና በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የታገዙ የሙዚቃ ሥራዎች፤ "ይፍጠሩ፣ ይወዳደሩ፣ ይሸለሙ" በሚል መርህ ለሚካሄደው ውድድር እንደሚቀርቡ ተገልጿል።።

ተወዳዳሪዎች ከ2 እስከ 5 ደቂቃ የሚረዝሙ እና ቢያንስ 70 በመቶው በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የተዘጋጁ የሙዚቃ ሥራዎችን ማቅረብ እንደሚኖርባቸው ተጠቁሟል።

ውድድሩ የሀገሪቱን የጥበብ ዘርፍ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0