ኢትዮጵያ በ2022 የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 75 በመቶ ለማድረስ ማቀዷን አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በ2022 የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 75 በመቶ ለማድረስ ማቀዷን አስታወቀች
ኢትዮጵያ በ2022 የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 75 በመቶ ለማድረስ ማቀዷን አስታወቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.03.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በ2022 የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 75 በመቶ ለማድረስ ማቀዷን አስታወቀች

ሀገሪቱ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን እየተካሄደ ባለው የ "ሚሽን 300" የኢነርጂ ኮንፈረንስ ላይ ብሔራዊ የኢነርጂ ስትራቴጂዋን ይፋ አድርጋለች።

ስትራቴጂው በኤሌክትሪክ ተደራሽነት፣ በንፁህ የምግብ ማብሰያ ዘዴዎች፣ በኃይል መሠረተ ልማት፣ በክልላዊ የኃይል ንግድ እና በግል ዘርፍ ተሳትፎ ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል።

በዚህም በቀጣይ አራት ዓመታት የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ሽፋን 75 በመቶ በማድረስ፤ ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ዜጎች የኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተቀምጧል።

በ2022 የሀገሪቱን አጠቃላይ የኃይል ማመንጨት አቅም ወደ 14 ሺ ሜጋ ዋት ለማሳደግ ግብ መቀመጡም ተገልጿል።

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች እና የልማት አጋሮች ለዚህ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0