10,934 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች ዕጩዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመፎካከር ተመዘገቡ
13:51 07.03.2026 (የተሻሻለ: 14:24 07.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
10,934 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች ዕጩዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመፎካከር ተመዘገቡ
ከጠቅላላ ዕጩዎች ውስጥ 2,198ቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ 8,736ቱ ደግሞ ለክልል ምክር ቤቶች እንደሚወዳደሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
በምርጫው 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 73 የግል ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
🪧 አጠቃላይ የዕጩዎች ምዝገባ ሂደት በዘመናዊ የዲጂታል ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ የዕጩዎች ስም በየምርጫ ክልላቸው ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
በተያያዘም የመራጮች ምዝገባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን መራጮች በ "ምርጫዬ" ሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት በቤታቸው ሆነው መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ 7ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻ እንደሚካሄድ መገለጹ ይታወሳል።
ምሥሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምጽ መስጫ ቀን ቁሳቁሶች እሸጋ እና ስርጭት ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X