የዲጂታል፣ የርቀት እና የፍሪላንስ ገቢን በግብር ሥርዓት ውስጥ የሚያካትት አዲስ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዲጂታል፣ የርቀት እና የፍሪላንስ ገቢን በግብር ሥርዓት ውስጥ የሚያካትት አዲስ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጀ
የዲጂታል፣ የርቀት እና የፍሪላንስ ገቢን በግብር ሥርዓት ውስጥ የሚያካትት አዲስ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.03.2026
ሰብስክራይብ

የዲጂታል፣ የርቀት እና የፍሪላንስ ገቢን በግብር ሥርዓት ውስጥ የሚያካትት አዲስ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጀ

የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017ን ለማስፈጸም የሚያስችል እና በዲጂታል አማራጮች የሚገኙ ገቢዎችን ያካተተ አዲስ የገቢ ግብር ረቂቅ ደንብ ማዘጋጀቱን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ማንን ይመለከታል፦ ረቂቅ ደንቡ በኢትዮጵያ ነዋሪ ሆነው በዲጂታል፣ በፍሪላንስ ወይም በርቀት የሥራ ዘዴ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ምንጭ ገቢ የሚያገኙ ግለሰቦች የገቢ ግብር እንዲከፍሉ ይደነግጋል፡፡

ምን ይጠበቅባቸዋል፦ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የሚያገኙትን ማንኛውንም ገቢ (በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት) በትክክል የሚገልጽ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ይጣልባቸዋል።

ግዴታ፦ ለዲጂታል ፈጣሪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ ኩባንያዎች፣ ስለ ተከፋዮቹ ማንነትና የተከፈለውን ገንዘብ መጠን በየሩብ ዓመቱ ለታክስ ባለሥልጣኑ ሪፖርት የማድረግ ግዴታ ይኖርባቸዋል ተብሏል።

ማንኛውም ፍላጎት ያለው አካል በረቂቅ ደንቡ ላይ ያለውን አስተያየት እስከ መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በጽሑፍ ወይም በኢሜል እንዲያቀርብ የገንዘብ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0