ዚምባብዌ የውጭ ኩባንያዎች እስከ 2027 ከሀገር በቀል ባለሀብቶች ጋር ካልተጣመሩ እንዲወጡ የሚያዝ አዲስ ገደብ ጣለች
18:31 06.03.2026 (የተሻሻለ: 18:34 06.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ የውጭ ኩባንያዎች እስከ 2027 ከሀገር በቀል ባለሀብቶች ጋር ካልተጣመሩ እንዲወጡ የሚያዝ አዲስ ገደብ ጣለች
የፍትሕ ሚኒስትሩ ዚያምቢ ዚያምቢ ለፓርላማ እንደገለጹት፤ በዚምባብዌ ሕጋዊ መመሪያ ቁጥር 215 መሠረት ለዚምባብዌ ዜጎች ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የውጭ ኩባንያዎች እስከ 2027 ድረስ ከሀገር በቀል ባለሀብቶች ጋር መጣመር አልያም ሥራቸውን አቁመው መውጣት ይኖርባቸዋል።
ሚኒስትሩ የጠቀሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
◻ አዲሱ ደንብ የዜጎችን የኢኮኖሚ ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ሲሆን የተወሰኑ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለዚምባብዌ ዜጎች ይከለክላል።
◻ መንግሥት ከኢንዱስትሪ እና ንግድ ሚኒስቴር እንዲሁም ከንግድ ባለድርሻ አካላት ጋር በመካከር የአፈጻጸም ሂደቱን ይገመግማል፡፡
◻ ይህ ፖሊሲ ለኩባንያዎች በቂ የማስተካከያ ጊዜ በመስጠት፤ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎችን በዚምባብዌ ዜጎች እጅ ለማስገባት የሚደርገው ሰፊ ጥረት አካል ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X