ኢትዮጵያና ናይጄሪያ የዳንጎቴ ሲሚንቶ የ1 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገለፀ
17:05 06.03.2026 (የተሻሻለ: 17:14 06.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያና ናይጄሪያ የዳንጎቴ ሲሚንቶ የ1 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገለፀ
ከአፍሪካ ቀዳሚ የሲሚንቶ አምራች የሆነው ዳንጎቴ ሲሚንቶ፤ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ የማምረት አቅሙን በ45 በመቶ ለማሳደግ የ1 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ እቅድ ይፋ አድርጓል።
ይህ የማስፋፊያ ሥራ በዋነኝነት ኢትዮጵያንና ናይጄሪያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን እንደሚያካትት ተመላክቷል።
ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ያለውን የ55.17 ሚሊዮን ቶን ዓመታዊ ምርት ወደ 80 ሚሊዮን ቶን ለማድረስ ማቀዱ ተጠቁሟል።
አዳዲስ ፋብሪካዎችን ለመገንባትና ነባሮቹን ለማስፋፋት ከቻይናው 'ሲኖማ' ኩባንያ ጋር የ1 ቢሊዮን ዶላር ውል እንደተፈራረመ ሚዲዎች ዘግበዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X