በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል "የኢትዮጵያውያን መንደር" ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ
16:45 06.03.2026 (የተሻሻለ: 16:54 06.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል "የኢትዮጵያውያን መንደር" ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ
በከምባታ ዞን የሚገኘውን የሀምበሪቾ ቱሪስት መዳረሻ ለማልማት የታለመውና "የኢትዮጵያውያን መንደር" የተሰኘውን ፕሮጀክት ግንባታ በይፋ ለማስጀመር የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል።
ፕሮጀክቱ የዓድዋ አርበኞች ሐውልት፣ 30 ጎጆዎች፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የሕፃናት መጫወቻና መማሪያ ክፍሎችን እንዲሁም ሌሎች የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካትታል ተብሏል።
“ዓላማው የክልሉን የቱሪስት መዳረሻዎች በማልማት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግና የሁሉንም ክልሎች ባሕልና እሴት የሚገልጽ መንደር መገንባት ነው” ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ተናግረዋል።
የክልሉ መንግሥት ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ርዕሰ መስተዳደሩ አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X