የአውሮፓ ኅብረት የኃይል ዘርፍ ሙሉ በሙሉ የመፈራረስ አደጋ ተጋርጦበታል - የሩሲያ ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ
16:13 06.03.2026 (የተሻሻለ: 16:44 06.03.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአውሮፓ ኅብረት የኃይል ዘርፍ ሙሉ በሙሉ የመፈራረስ አደጋ ተጋርጦበታል - የሩሲያ ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ
"ይህ የአዲሱ ዘመን መጀመሪያ ነው፡፡ በአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን፣ በአውሮፓ ኅብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ካጃ ካላስ እና በሌሎች 'ሩሲያ-ጠል' ረብ የለሽ ውሳኔ አውሮፓ ሙሉ በሙሉ የኃይል መፈራረስ እና ኪሳራ የገባችበት ወቅት ነው" ሲሉ ኪሪል ዲሚትሪቭ በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
አክለውም የአውሮፓ ኅብረት የሩሲያን የኃይል አቅርቦት በመተዉ "በእራሱ እግር ላይ ደጋግሞ በመተኮሱ አሁን ላይ የሚተኮስበት እግር እንኳ አልቀረውም" ብለዋል።
ሰኞ የአውሮፓ የጋዝ ዋጋ 50 በመቶ በመጨመር ለ1,000 ኩብ ሜትር 590 ዶላር ደርሷል። በነጋታው ደግሞ 45 በመቶ በመጨመር እ.አ.አ ከየካቲት 2 ቀን 2023 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ1,000 ኩብ ሜትር ከ780 ዶላር በላይ ሆኗል።
ይህ የዋጋ ጭማሪ የመጣው በዓለም ላይ ካሉ ሦስት ከፍተኛ የተፈጥሮ ጋዝ አምራቾች እና ላኪዎች አንዷ የሆነችው ኳታር፤ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት ምክንያት በሁሉም የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ተቋሞቿ ምርት ማቋረጧን ካስታወቀች በኋላ ነው።
ዲሚትሪቭ ባጋሩት የ2025 ቪዲዮ፤ ቮን ደር ሌየን የአውሮፓ ኅብረት እስከ 2027 መጨረሻ ሙሉ በሙሉ የሩሲያን ጋዝ ማስገባት ለማቆም እንዳቀደ ሲያሳውቁ ይታያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia